የኮቪድ-19 ክትባትዎን መውሰድ: ምን መጠበቅ ይቻላል | Getting your COVID-19 vaccine: What to expect

ክትባቶች የኮቪድ-19 ወረርሺኝን መዋጋት እና የማህበረሰባችንን ደህንነት እና ጤና ለመጠበቅ ከምንችልባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው።

መከላከያ

የኮቪድ-19 ክትባቶች ኒውዚላንድ ውስጥ ነጻ እና ለሁሉም የሚገኙ ናቸው።

ክትባቶች ጤናዎን ይጠብቃሉ እና ከሰውነትዎ ተፈጥሯዊ መከላከያዎች ጋር አብሮ በመስራት በሽታን ይከላከላሉ ስለዚህ ተጋላጭ ከሆኑ፣ ቫይረሱን ለመዋጋት ዝግጁ ኖት።

የኮቪድ-19 ክትባት በሽታ የመከላከል አቅምዎን በመቀስቀስ የኮቪድ-19ን ለመዋጋት የሚሰሩ አንቲቦዲዎችን እና የደም ህዋሶችን እንዲያመርት በማድረግ ነው የሚሰራው።

የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ከቫይረሱ ተጽእኖዎች ራስዎን ለመጠበቅ ሊወስዱት የሚችሉት አስፈላጊ እርምጃ ነው።

አንዴ ከተከተቡ በኋላ፣ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ጥንቃቄዎችን መውሰድዎን ይቀጥሉ። እጅዎን በደንብ ይታጠቡ እንዲሁም ያድርቁ። በክርንዎ ሸፍነው ያስሉ ወይም ይስነጥሱ እንዲሁም ህመም ከተሰማዎት በቤትዎ ይቆዩ። ይህ እርስዎን፣ የእርስዎን ውሃኑ (whānau) እና ሌሎችንም ለመጠበቅ ይረዳዎታል።

የኮቪድ መከታተያ መተግበሪያውን መጠቀም ይቀጥሉ፤ የስልክዎን ብሉቱዝ ያብሩ፤ እንዲሁም የፊት መሸፈኛ ወይም ማስክ ማድረግ ሊያስፈልጎ ይችላሉ።

ደህንነት

ሜድሴፍ (Medsafe) ኒውዚላንድ ውስጥ አንድ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ የሚሰጠው ጥቅም ላይ ለመዋል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። ሁሉም የኮቪድ-19 ክትባቶች በተመሳሳይ የደህንነት ምርመራ ውስጥ ያልፋሉ እናም ተመሳሳይ ጤናማ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው።

የፋይዘር ክትባት

ይህ ክትባት ኮቪድ-19ን አያስይዝዎትም። ቢያንስ በሶስት ሳምንታት ልዩነት፣ ሁለት የክትባት ዶዞች ያስፈልግዎታል። ምርጥ የበሽታ መከላከል እንዳልዎት እርግጠኛ ለመሆን፣ ሁለቱንም የክትባት ዶዞች መውሰድዎን ያረጋግጡ።

በቀጠሮ መገኘት ካልቻሉ፣ በተቻለ ፍጥነት እንደገና ቀጠሮ ይያዙ።

ክትባት ከመውሰድዎ በፊት ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች

ከዚህ በፊት ለማንኛውም ክትባት ወይም መርፌ ከባድ ወይም ፈጣን የአለርጂ ግብረ መልስ ከነበርዎት፣ ከክትባት ሰጪዎ ጋር እባክዎ ይወያዩበት።

የደም ማቅጠኛ መድሀኒቶች ላይ ከሆኑ ወይም የደም መፍሰስ ህመም ካለብዎት፣ እባክዎ ክትባት ሰጪዎ እንዲያውቅ ያድርጉ።

ነፍሰጡር ከሆኑ፣ እባክዎ ክትባት ሰጪዎ፣ GP ወይም አዋላጅ ነርስዎን ያነጋግሩ።

በዚህ ጊዜ ከ 16 አመት በታች ለሆኑ ሰዎች የፋይዘርን ክትባት እየሰጠን አይደለም።

የኮቪድ-19 ምልክቶች ካልዎት፣ ይመረመሩ እና ውጤቶችዎን እስኪቀበሉ በቤትዎ ይቆዩ። የምርመራ ውጤትዎ ኔጌቲቭ ከሆነ በኋላ ክትባት መውሰድ ይችላሉ።

ክትባት ከወሰድኩ በኋላ ምን ይፈጠራል?

የህክምና ሰራተኞች ከባድ የአለርጂ ግብረ መልስ እንደሌልዎት ማረጋገጥ እንዲችሉ ክትባት ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ 20 ደቂቃ መጠበቅ አለብዎት።

ለክትባቶች ወይም ሌሎች ምርቶች ከባድ ግብረ መልሶች ከነበርዎት፣ ወይም ክትባት ከወሰዱ በኋላ ረዥም መንገድ መጓዝ ካለብዎት፣ ረዘም ላለ ጊዜ መታየት ሊኖርብዎት ይችላል።

ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች

እንደሁሉም መድሀኒቶች፣ ክትባቱ የተወሰኑ ሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። እነዚህ የተለመዱ ናቸው፤ ብዙውን ጊዜ አነስተኛ እና ብዙ ጊዜ የማይቆዩ እንዲሁም ሁለተኛ ዶዝ ከመውሰድ ወይም የእለት ከእለት ህይወትዎን ከማካሄድ አያስቆምዎትም።

በጣም የተለመዱ ሪፖርት የተደረጉ ግብረ መልሶች መርፌው የተወጋበት ቦታ ላይ ህመም ፣ ራስ ምታት እና የድካም ወይም የመዛል ስሜት መሰማት ናቸው።

የጡንቻ ህመሞች፣ የጤነኝነት ስሜት በአጠቃላይ አለመሰማት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ትኩሳት፣ የመገጣጠሚያ ህመም እና ማቅለሽለሽም ሊከሰቱ ይችላሉ። ይህ ክትባቱ እየሰራ እንደሆነ ያሳያል። እነዚህ በብዛት ሪፖርት የሚደረጉት ከሁለተኛው ዶዝ በኋላ ነው።

የተወሰኑት የጎንዮሽ ጉዳቶች የመንዳት ወይም ማሽኖችን የመጠቀም ችሎታዎን በጊዜያዊነት ሊጎዱ ይችላሉ።

ከባድ የአለርጂ ግብረ መልሶች ይከሰታሉ ነገር ግን በጣም ያልተለመዱ ናቸው። የእኛ ክትባት ሰጪዎች እነዚህን ለመቆጣጠር የሰለጠኑ ናቸው።

ተጨማሪ ድጋፍ እና መረጃ

አዲስ ተከታታይ ሳል፣ ከፍተኛ ሙቀት/ትኩሳት ወይም የመቅመስ ወይም የማሽተት መደበኛ የስሜት ህዋሳትን ማጣት ወይም መለወጥ የመሳሰሉ ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ሊሆኑ የሚችሉ ምልክቶች ከተሰማዎት፣ ቤት ውስጥ ይቆዩ እና የኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ።

ስለ ምልክቶችዎ እርግጠኛ ካልሆኑ ወይም እየባሱ ከሄዱ፣ በ 0800 358 5453 የጤና መስመር ላይ ይደውሉ።

ስለ ደህንነትዎ አስቸኳይ ስጋት ካልዎት፣ 111 ላይ ይደውሉ፤ እንዲሁም በትክክል እርስዎን መመርመር እንዲችሉ የኮቪድ-19 ክትባት እንደወሰዱ ለእነርሱ መናገርዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

ትክክለኛ መረጃን ማግኘት ጠቃሚ ነው።

ማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ካሉ የተሳሳቱ መረጃዎች ይጠንቀቁ።

ትክክለኛ እና የታመነ መረጃን ከሚከተሉት ማግኘት ይችላሉ:

covid19.govt.nz/vaccine

health.govt.nz/covid-vaccine (external link)

ወይም 0800 358 5453 የጤና መስመር ላይ ይደውሉ።