ክትባት ከወሰዱ በኋላ | After your vaccination

ምን ሊሰማዎት ይችላል ምን ሊረዳዎት ይችላል ይህ መቼ ሊጀምር ይችላል
መርፌው የተወጋበት ቦታ ላይ ያለ ህመም፣ ራስ ምታት እና የድካም እና የመዛል ስሜት መሰማት።

እነዚህ በጣም የተለመዱ ሪፖርት የሚደረጉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ናቸው።
መርፌው የተወጋበት ቦታ ላይ ቀዝቃዛ፣ እርጥብ ልብስ፣ ወይም የበረዶ ጥቅል ለአጭር ጊዜ ያድርጉ።

መርፌው የተወጋበትን ቦታ አይፈትጉት ወይም አይሹት።
ከ 6 እስከ 24 ሰአታት ውስጥ 
የጡንቻ ህመሞች፣ በአጠቃላይ የጤነኝነት ስሜት አለመሰማት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ትኩሳት፣ የመገጣጠሚያ ህመም እና ማቅለሽለሽም ሊከሰቱ ይችላሉ። እረፍት ይውሰዱ እና ብዙ ፈሳሾችንም ይጠጡ።

ፓራሲታሞል ወይም አይቡፕሮፌን ሊወሰድ ይችላል፤ የአምራቹን መመሪያዎች ይከተሉ።

ምልክቶችዎ እየባሱ ከሄዱ ከጤና ባለሙያዎ ምክር ይጠይቁ።
ከ 6 እስከ 48 ሰአታት ውስጥ 

እንደሁሉም መድሀኒቶች፣ ክትባቱ የተወሰኑ ሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላል። ይህ የሰውነታችን መደበኛ ምላሽ ነው እናም ክትባቱ እየሰራ እንደሆነ ያሳያል።

የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ብዙውን ጊዜ አነስተኛ እና ብዙ ጊዜ የማይቆዩ እንዲሁም ሁለተኛ ዶዝ ከመውሰድ ወይም የእለት ከእለት ህይወትዎን ከማካሄድ አያስቆምዎትም።

የክትባቱ ሁለተኛ ዶዝ ከወሰዱ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳቶች በጣም የተለመዱ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከባድ የአለርጂ ግብረ መልሶች ሊከሰቱ ይችላሉ ነገር ግን በጣም ያልተለመዱ ናቸው። የኒውዚላንድ ክትባት ሰጪዎች እነዚህን ለመቆጣጠር የሰለጠኑ ናቸው። የተወሰኑት የጎንዮሽ ጉዳቶች የመንዳት ወይም ማሽኖችን የመጠቀም ችሎታዎን በጊዜያዊነት ሊጎዱ ይችላሉ። በድንገት እንኳን ይህ ከተከሰተ፣ እባክዎ ከአሰሪዎ ጋር ይወያዩበት።

አዲስ ተከታታይ ሳል፣ ከፍተኛ ሙቀት/ትኩሳት ወይም የመቅመስ ወይም የማሽተት መደበኛ የስሜት ህዋሳትን ማጣት ወይም መለወጥ የመሳሰሉ ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ሊሆኑ የሚችሉ ምልክቶች ከተሰማዎት፣ ቤት ውስጥ ይቆዩ እና የኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ።

ለወሰዱት የኮቪድ-19 ክትባት ያልተጠበቀ ግብረ መልስ ካልዎት፣ የእርስዎ ክትባት ሰጪ ወይም የጤና ባለሙያ ይህንን ለአስከፊ ግብረ መልሶች መቆጣጠሪያ ማእከል (Centre for Adverse Reactions Monitoring - CARM) ሪፖርት ማድረግ አለበት።

በ CARM ድረገጽ ልይ ያለውን የኦንላይን ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ በመጠቀም ማንኛውንም ያልተጠበቁ ግብረ መልሶች ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ: otago.ac.nz/carm (external link)

ስለ ምልክቶችዎ እርግጠኛ ካልሆኑ ወይም እየባሱ ከሄዱ፣ GPዎን ያነጋግሩ ወይም 0800 358 5453 (external link) የጤና መስመር ላይ ይደውሉ።

ስለ ደህንነትዎ አስቸኳይ ስጋት ካልዎት፣ 111 (external link) ላይ ይደውሉ፤ እንዲሁም በትክክል እርስዎን መመርመር እንዲችሉ የኮቪድ-19 ክትባት እንደወሰዱ ለእነርሱ መናገርዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

ክትባቶች ከፍኝ እና ኢንፍሉዌንዛ ከመሳሰሉ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በሁሉም እድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጠበቅ ይረዳሉ።

እርስዎ እና የእርስዎ ውሃኑ (whānau) ስለ ክትባቶችዎ ከጤና አቅራቢዎ ጋር በመነጋገር ወቅታዊ መረጃ ማግኘትዎን ያረጋግጡ። ለተጨማሪ መረጃ health.govt.nz/immunisation (external link) ን ይጎብኙ ።

ሌሎች ማንኛውንም ክትባቶች ከመውሰድዎ በፊት ሁለተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለሁለት ሳምንታት መጠበቅ አለብዎት።